Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ለሕፃናት የቤት ለቤት ክትባት መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ከ450 ሺህ በላይ ሕፃናት የቤት ለቤት ክትባት መሰጠት መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ለአንድ ሳምንት የሚቆየውን የክትባት ዘመቻ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሙሴ አህመድ ከዓለም ጤና ድርጅትና ከዩኒሴፍ ተወካዮች ጋር በጅግጅጋ ከተማ አስጀምረዋል፡፡

ዶ/ር ሙሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በዘመቻው የፖሊዮ፣ የመንጋጋ ቆልፍ እና ሌሎች ከ10 በላይ ለሚሆኑ በሽታዎች የመከላከያ ክትባት ይሰጣል፡፡

ለዘመቻው ስኬታማነት ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ በማስከተብ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀርበዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.