Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ በጋምቤላ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጋምቤላ ክልል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አከናወኑ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ የጀመርነውን የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በጋምቤላ ክልል አስቀጥለናል ብለዋል፡፡

መርሐ ግብሩን ዛሬ በጋምቤላ ክልል በአኙዋሃ ዞን በዲማ ወረዳ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ማከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በዚህ መርሐ ግብር ዓለምን ያስደመመ ስኬት አስመዝግበናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ለዚህ ድል ደግሞ መንግስት እና ህብረተሰቡ በጋራ ያደረጉት ርብርብና ቁርጠኝነት ወሳኝ ነበር ነው ያሉት፡፡

የአረንጓዴ ልማት በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል እና ለሌሎች ስራዎች እንደማስፈንጠሪያነት ያገለግል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል ሚናውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.