Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰሮቹ አባት እና ልጅ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሮፌሰር ባዬ ይማም (አባት) እና ፕሮፌሰር ቃለአብ ባዬ ይማም (ልጅ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያፈራቸው ምሁራን ናቸው፡፡

ሁለቱም የከፍተኛ ትምህርት ሕይወታቸውን በአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጀምረው በሞያቸው ዩኒቨርሲቲውን እያገለገሉና ተተኪ ምሁራንን እያፈሩ ይገኛሉ፡፡

ፕሮፌሰር ባዬ ይማም 44 ዓመታትን እንዲሁም ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ 15 ዓመታትን በመምህርነት፣ በተመራማሪነት፣ እንዲሁም በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች ያገለገሉ እና እያገለገሉ የሚገኙ ምሁራን ናቸው።

ሁለቱም የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን በሰሩ ልክ በ10ኛው ዓመት የሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማግኘታቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ በዘንድሮው ዓመት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከሰጣቸው ምሁራን መካከል ናቸው።

ማዕረጉ የተሰጣቸው በማስተማር ውጤታማነት፣ ባሳተሟቸው 13 ጥናታዊ ጹሑፎች፣ ለማህበረሰብ ላበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የተቋም አስተዳደር ድምር ውጤት መሆኑ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.