Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ4 የፈጠራ ውጤቶች የፓተንት መብት ተሰጠው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ላበለጸጋቸው አራት የፈጠራ ውጤቶች ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የፓተንት መብት ማግኘቱን አስታወቀ።

ለኢንስቲትዩቱ የተሰጠው የፓተንት መብት ሰው ሰራሸ አስተውሎት ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የስኳር በሽታ አይነት፣ የጡት ካንስር አይነት የሚለይ፣ የህፃናት የቆዳ በሽታ ልየታ የሚሰራ ሥርዓት እንዲሁም የቡና ቅጠል በሽታ ልየታ የሚያደርግ የፈጠራ ውጤቶች እንደሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል የፓተንት መብት የእውቅና ምስክር ወረቀት መቀበላቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.