Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ከቤልጂየም የሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ፈረንሳይና ቤልጂየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚህ መሰረትም ምሽት 1 ሰዓት ላይ ፈረንሳይ እና ቤልጂየም በዱሲልዶርፍ አሬና ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

በጨዋታው በተለይም የፈረንሳዩ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ እና የቤልጂየሙ የፊት መስመር ተሰላፊ ሮሜሎ ሉካኩ ቡድናቸውን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማሳለፍ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በፊፋ ወቅታዊ የብሔራዊ ቡድኖች የእግር ኳስ ደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከአውሮፓ አህጉር ፈረንሳይ ቀዳሚ ስትሆን÷ ቤልጂየም ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በተጨማሪም ፖርቹጋል ከስሎቬኒያ ምሽት4 ሰዓት ላይ በፍራንክፈርት አሬና ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

በምድብ ስድስት ጥሎ ማለፉን 6 ነጥብ በመያዝ በቀዳሚነት የተቀላቀለችው ፖርቹጋል ጨዋታውን የማሸፍ ግምት ተሰጥቷታል፡፡

ጥሎ ማለፉን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀላቀለችው ስሎቬኒያ ደግሞ በምድብ ሶስት በ3 ነጥብ ምርጥ 3ኛ ሆና ነው ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለችው፡፡

በምሽቱ ጨዋታ ስሎቬኒያ በአውሮፓ ዋንጫ ሌላ አዲስ ታሪክ ለራሷ ለማስመዝገብ ከፍተኛ ፉክከር እንደምታደርግ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.