በሸገር ከተማ 315 ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር በ2016 በጀት ዓመት ከተያዙ 406 ፕሮጀክት 315ቱ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ጉዮ ገልገሎ እንደገለጹት÷በበጀት ዓመቱ 96 ነባር እና 310 አዳዲስ ፕሮጀክቶች ታቅደው በስፋት ሲሰራባቸው ቆይቷል።
በዚህ መሰረትም የአዳዲስ ት/ቤቶች ግንባታ፣ 500 አልጋ የሚይዝ አዲስ ሆስፒታል ፣ የመጠጥ ውሃ ሽፋንን ወደ 66 በመቶ የሚሳድጉ እና መሰል ሥራዎች ፕሮጀክት ተቀርጾ እንደተሰራባቸው አንስተዋል፡፡
ዲጂታል ሸገርን እውን ያደርጋል የተባለውፕሮጀክት መጠናቀቁንም ነው ምክትል ከንቲባው ያመላከቱት፡፡
በ2016 በጀት ዓመት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች እንደ ፕሮጀክት ባህሪያቸው በ2017 በጀት ዓመት እንደሚጠናቀቁም ጠቁመዋል፡፡
በሜሮን ሙሉጌታ እና ለሊሴ ተስፋዬ