Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል አዳማ ከተማን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል አዳማ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የመቻልን የማሸነፊያ ግቦች ሽመልስ በቀለ፣ አህመድ ረሺድ (በራስ ላይ) እና በረከት ደስታ አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም መቻል ለዋንጫ የሚያደርገውን ፉክክር ማጠናከር ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ61 ነጥብ ሲመራ መቻል ደግሞ በ60 ነጥብ በሁለተኛነት ይከተላል፡፡

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ ክለብ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ በሚደረጉ ጨዋታዎች የሚለይ ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.