የሸነን አፍሪካ አህጉር አቀፍ የፋሽን፣ የቱሪዝምና ስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው አህጉር አቀፍ የፋሽን፣ የቱሪዝም እና የስፖርት ፌስቲቫል ለተከታታይ 3 ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጠናቅቋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ የዘርፉ ሚኒስትር ዴዔታዎችና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ ታድመዋል።
በፌስቲቫሉ ሀገር በቀል ምርቶችን ከማስተዋወቅ ባለፈ በሀገራዊ ገጽታ ግንባታ ላይ የልምድ ልውውጥ መካሄዱ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም የአፍሪካና የኢትዮጵያ አንጋፋ ተጫዋቾች መካከል ስፖርታዊ ጨዋታዎችን ጨምሮ በኪነጥበብ ዘርፍ የፋሽን ሾው ትዕይንትና መሰል ሁነቶች እንደተካሄዱ ተገልጿል፡፡
ሸነን አፍሪካ አህጉር አቀፍ የፋሽን፣የቱሪዝም እና የስፖርት ፌስቲቫል የቀድሞ ታዋቂ የአፍረካ እግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ተዋናዮች እና የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንደተሳተፉበት የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሸነን አፍሪካ አህጉር አቀፍ የፋሽን፣ የቱሪዝም እና የስፖርት ፌስቲቫል ለተሳተፉ አካላት የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት በማበርከት ፌስቲቫሉ መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡