ከ545 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ወደብ ደረሰች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 545 ሺህ 300 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቃል፡፡
ይህን ተከትሎም ኮርፖሬሽኑ ለ2016/17 የምርት ዘመን ከውጭ እያስገባ የሚገኘው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ወደ 17 ሚሊየን 494 ሺህ 840 ኩንታል ከፍ ማለቱ ተገልጿል፡፡
እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስም 15 ሚሊየን 278 ሺህ 943 ኩንታል ማዳበሪያ ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል ተጨማሪ 785 ሺህ 980 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡