Fana: At a Speed of Life!

“መቻል ለ ኢትዮጵያ” የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በስኬት ተጠናቀቀ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “መቻል ለ ኢትዮጵያ” የተሰኘውና በመስቀል አደባባይ የተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በስኬት ተጠናቀቀ።

መነሻውን እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው “መቻል ለኢትዮጵያ” የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጀነራል አለምሸት ደግፌ÷ መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ ባሻገር የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ከፍ ያደረጉ ብርቅዬ አትሌቶችን ያፈራ ተቋም ነው ብለዋል።

በኦሎምፒክ የመጀመሪያ ወርቅ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ያስገኘው ሻምበል አበበ ቢቂላ የመቻል ስፖርት ክለብ ትሩፋት እንደሆነም ለአብነት ጠቀሰዋል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የስፖርት ውድድር መድረኮች ለተቀዳጀቻቸው ድሎች መቻል ስፖርት ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከተም አስታውሰዋል።

የመቻል 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚገኝ ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.