ስዊዘርላንድ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ስዊዘርላንድ የ2020 ሻምፒዮናዋን ጣልያንን 2 ለ 0 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡
ጎሎቹንም ፍሩለር እና ቫርጋስ በመጀመሪያው እና በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ስዊዘርላንድ በሩብ ፍጻሜው ከእንግሊዝና ስሎቫኪያ አሸናፊ ጋር የምትፋለም ይሆናል፡፡
የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ቀሪ መርሐ-ግብር ሲቀጥል ምሽት አራት ሠዓት ላይ አስተናጋጇ ጀርመን ከዴንማርክ ይጫወታሉ፡፡
የጀርመንና ዴንማርክ አሸናፊ በሩብ ፍጻሜው ከስፔን እና ጆርጂያ አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።