Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 44 ከፍ በማድረግ ከአዳማ ከተማ እኩል 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

እንዲሁም ወላይታ ድቻ በ34 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ 12 ሠዓት ላይ በተከናወነ የሸገር ደርቢ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

በጨዋታው ሞሐመድ ናስር ኢትዮጵያ ቡናን ቀዳሚ ማድረግ ቢችልም፤ ፍሪምፖንግ ክዋሜ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሽንፈት ታድጓል፡፡

በውጤቱ መሰረትም ፈረሰኞቹ ነጥባቸውን 45 በማድረስ 5ኛ ደረጃ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና በ51 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.