አቶ ሽመልስ አብዲሳ የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በምዕራብ ወለጋ ዞን የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይም የፌደራል እና የኦሮሚየ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በተመሳሳይ ርዕሰ መሥተዳድሩ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ የጊቤ ዴዴሳ አርሶ አደሮች ዩኒየን እያስገነባ ያለውን የዱቄት ፋብሪካጎብኝተዋል፡፡
አሁን ላይ 101 ሚሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገበው ዩኒየኑ÷ ተጨማሪ የተለያዩ የግብርና ማቀነባበሪያ ሥራዎችን ለማስጀመር ግንባታ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በማርታ ጌታቸው