Fana: At a Speed of Life!

የዙይ-ሐሙሲት የመጠጥ ውኃ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው የሐሙሲት ከተማ የመጠጥ ውኃ ፕሮጄክት ግንባታ ሲጠናቀቅ ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገለፀ፡፡

ፕሮጄክቱ የሐሙሲት ከተማን ጨምሮ ሌሎች 11 ቀበሌዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡

ግንባታውን በሁለት ዓመታት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ሲሆን÷ አሁናዊ የግንባታ አፈጻጸሙም 18 በመቶ መድረሱን የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከሚያስፈልገው 1 ነጥብ 13 ቢሊየን ብር 339 ነጥብ 6 ሚሊየኑ በክልሉ መንግሥት ቀሪው ደግሞ በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር (ሲ አር ዋሽ) መሸፈኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.