Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲትዩቱ በዓመት 300 ሚሊየን ዶዝ የእንስሳት ክትባት እያመረተ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በዓመት 300 ሚሊየን ዶዝ የእንስሳት ክትባት እያመረተ መሆኑን አስታውቋል።

የብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረነው።

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ አባይነህን ጨምሮ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላት እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዶ/ር ታከለ በወቅቱ እንዳሉት፥ የብሄራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የእንስሳት ሃብት ዘርፉን ከመደገፍና የውስጥ ቴክኖሎጂ አቅምን ከመገንባት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

ኢንስቲትዩቱ የአርብቶ አደሩ ዋነኛ ችግር የሆኑትን ተላላፊ የእንስሳት በሽታዎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ የእንስሳት ክትባቶችን እያመረተ መሆኑንም አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅትም 23 በባክቴሪያ እና በቫይረስ ለሚመጡ የእንስሳት በሽታዎች የመከላከያ ክትባት እያመረተ ነው ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ በዓመት ውስጥም በምርምርና ጥናት የተደገፈ 300 ሚሊየን ዶዝ የእንስሳት ክትባት ያመርታል ነው ያሉት።

ከውጪ የሚገዙ የእንስሳት መድሃኒቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በቀጣይም የኢንስቲትዩቱን ክትባት የማምረት አቅም ለማሳደግ በትኩረት በመስራት ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም አዳዲስ ክትባቶችን ለማምረት የፋብሪካ ማስፋፊያ ስራ በቅርቡ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.