የአዲስ አበባ ካቢኔ የተለያዩ አዳዲስና ነባር ደንቦችን ለማሻሻል የቀረቡ ረቂቆችን መርምሮ አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 15ኛ መደበኛ ስብሰባው የከተማ አስተዳደሩ እየተገበረ ያለውን የተቋማት ሪፎርም ተከትሎ ለከተማው ነዋሪ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የተለያዩ አዳዲስ እና ነባር ደንቦችን ለማሻሻል የቀረቡ ረቂቆችን መርምሮ አፅድቋል።
በዚህም መሰረት:-
- የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር መመሪያ፣
- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሠራተኛ የስራ ልብስ አለባበስና እና ጌጣጌጥ አጠቃቀም የአፈጻጸም ደንብ ፣
- የመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ደንብ፣
- የህብረት ስራ ማህበራ አደረጃጀትና አሰራር ደንብ፣
- የህብረት ስራ ማህበራት የፋይናንስና ግዥና የንብረት አስተዳደር ደንብ፣
- የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ፣
- የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት እንደገና ለማቋቋም በተዘጋጀ ደንብ፣
- የኤግዚብሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ እንዲሁም
- የከነማ መድኃኒትና የህክምና መሳሪያ አቅራቢ ድርጅት እንደገና መቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡