Fana: At a Speed of Life!

በኢራን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢራን በቅርቡ በሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ባጡት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ቦታ አዲስ ፕሬዚዳንት ለመተካት አስቸኳይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መካሄድ ጀምሯል።

በዚህም በዛሬው ዕለት የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ከማለዳ ጀምሮ ተከፍተው ኢራናውያን ድምፅ መስጠት መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡

የምርጫ ጣቢያዎቹ ምሽት 12 ሰዓት ይዘጋሉ የተባለ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ የምርጫ ጊዜው ሊራዘም እንደሚችል ነው የተገለፀው፡፡

በምርጫው የኢራን ኢስላሚክ አብዮት መሪ አያቶላ ሰይድ አሊኻሜኒ ቴህራን በሚገኘው የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጽ ሰጥተዋል፡፡

አብዮታዊ መሪው በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ የዛሬው የምርጫ ቀን ኢራንን ለቀጣዩ ዓመታት የሚመራው ፕሬዚዳንት በኢራናውያን ድምፅ የሚወሰነበት ቀን ነው ብለዋል፡፡

ኢራን ከገጠማት የፖለቲካ ፈተና እንድትወጣ የዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው÷ በምርጫው መሳተፍ ያለበት ሁሉ ድምጹን እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡

በምርጫው ከ61 ሚሊዮን በላይ ኢራናውያን ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ መገለፁን የዘገበው ፕሬስ ቲቪ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.