Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ በ5 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ የሚሞላ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ አምራች ስታርት አፕ የሆነው ኒዮቦልት በአምስት ደቂቃ ጊዜ ውስጥ የሚሞላ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ፈጣን የተባለው ይህ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ በመጀመሪያ ሙከራው በአራት ደቂቃ ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ ባትሪ መሙላት መቻሉ ተገልጿል፡፡

ባትሪው ሙሉ ለሙሉ የተሞላ የኤሌክትሪክ መኪና እስከ 193 ኪሎ ሜትር ርቀት ሊጓዝ እንደሚችል ተነግሯል።

የባትሪ መሰረተ ልማት የኤሌክትሪክ መኪኖች በብዛት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ምክንያት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በእንግሊዝ ይፋ የሆነው ይህ አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ችግሩን በከፍተኛ ደረጃ ሊቀርፍ እንደሚችል ታምኖበታል፡፡

ቀደም ሲል ፈጣን የተባለው የቴስላ ሱፐር ቻርጀር የመኪና ባትሪ ሲሆን፤ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ሙሉ በሙሉ ሊሞላ እንደሚችል የገለጸው የቢቢሲ ዘገባ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.