Fana: At a Speed of Life!

ለሸነን አፍሪካ ፌስቲቫል የሚሳተፉ እንግዶች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሸነን አፍሪካ ፌስቲቫል የሚሳተፉ የክብር እንግዶች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሸነን አፍሪካ ፌስቲቫል ሳምንት ከነገ ጀምሮ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በፌስቲቫሉ የውጭ ሀገራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ተዋናዮች፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ሞዴሎች፣ የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም በሌሎች የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ግለሰቦች ይሰተፉሉ።

እንግዶች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አዲስ አበባ ሲገቡ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ ነፊሳ አልማኻዲ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የሚኒስቴርሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.