Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር በቀል እውቀቶችና መድሃኒቶች ትኩረት መስጠት ይገባል – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገር በቀል እውቀቶች እና መድሃኒቶች ትኩረት መስጠት ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን አውደ ርዕይ ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና ሌሎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትን ማስፋት ከውጭ የሚገባውን ምርት ለመተካት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን የጤና አገልግሎት ማስተካከል ያስችላል፡፡

ባለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በቆየው አውደ ርዕይ ከ100 በላይ የዘርፉ አምራቾች የተሳተፉ ሲሆን÷በቆይታው በ100 ሺህ ሰዎች መጎብኘቱ ተጠቁሟል፡፡

የፖሊሲ አውጪዎች፣ አስፈጻሚዎች፣ የዘርፉ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች፣ ባለሙያዎችና አምራቾች የፓናል ውይይቶች ጨምሮ የልምድ ልውውጥ እንደተደረገበትም ተመላክቷል።

በመድረኩ ዘርፉን በጋራ እና በጥምረት ለማሳደግ እንሰራለን በሚል የተለያዩ የሙያ ማህበራት ፌዴሬሽን ለመመስረት ተስማምተዋል፡፡

በኢትዮጵያ አሁን ላይ 36 በመቶ የሚሆነውን የመድሃኒትና የሕክምና ግብዓት በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን መቻሉም ተገልጿል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.