የአውሮፓ ኅብረት ለመስክ ሥራ የሚውሉ 18 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚደርገውን ጥረት ለማገዝ ለመስክ ሥራ የሚሆኑ 18 ተሽከርካሪዎችን ለፍትሕ ሚኒስቴር አበርክቷል።
የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ምክትል አምባሳደር ዴቪድ ክሪቫኔክ የቁልፍ ርክክብ አካሂደዋል።
የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል በሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ የ18 ተሽከርካሪዎች ግዥ መፈጸሙ ተገልጿል።
ተሽከርካሪዎቹ የኢትዮጵያን የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት የማሻሻል አስተዳደር ማዕቀፍ ውስጥ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የዜጎችን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለመመርመር የሚያከናውናቸውን የመስክ ሥራዎች በማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖራቸው መጠቀሱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡፡