Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን የምዕራፍ ሁለት 2ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ፣ የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ፍቃዱ ተሰማ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት÷ወለጋ የልማት ምድር፣ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ እና አብሮ የመኖር እሴት ተምሳሌት የሆነ ህዝብ የሚገኝበት ነው ብለዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ አራቱ የወለጋ ዞኖች ከፀጥታ ችግር መላቀቁን ገልጸው፤ የአካባቢውን ሰላም ማጽናት የክልሉ መንግስት ዋነኛ ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ጌቱ ገመቹ በበኩላቸው÷በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በክልሉ 4 ነጥብ 98 ቢሊየን ችግኝ የሚተከል መሆኑን ገልጸዋል።

ከሚተከለው ችግኝ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው የተቀናጀ ግብርና ተክል እንዲሁም ቀሪው 40 በመቶ ለደን እና ለውበት የሚውሉ ተክሎች ችግኝ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በማርታ ጌታቸው

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.