Fana: At a Speed of Life!

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ላይ ከፍ ያለ እድገት ታይቷል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተሰሩ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ላይ ከፍ ያለ እድገት መታየቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

“የክህሎትና ቴክኖሎጂ ልህቀት ለተወዳዳሪነት” በሚል መሪ ሀሳብ የቴክኖሎጂ፣ ክህሎት፣ ፈጠራ ስራዎች እንዲሁም ተግባራት ጥናት፣ ምርምር፣ ውድድር አውደ ርዕይ በሐዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት፤ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች በተለምዶ የሚሰሩ ተግባራትን በማቅለል ትልቅ ፋይዳ አላቸው።

በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተሰራው የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ከፍ ያለ እድገት መታየቱንም ተናግረዋል።

በክልሉ ያሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በርካታ የቴክኖሎጂ ተግባራት በማከናወን እንደ ሀገር ባሉ መድረኮች ተወዳዳሪ የሆኑ የፈጠራ ውጤቶችን ማበርከት መቻላቸውንም አንስተዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት በርካታ ዜጎችን በማሰልጠን ላይ እንደሚገኙም አመልክተዋል።

በብርሃኑ በጋሻውና ታመነ አረጋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.