Fana: At a Speed of Life!

ሮማኒያ፣ ቤልጂየም እና ስሎቫኪያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በምድብ 5 የተደለደሉት ሮማኒያ፣ ቤልጂየም እና ስሎቫኪያ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ምሽቱን በተካሄደው ጨዋታ በዚሁ ምድብ የሚገኙት ስሎቫኪያ እና ሮማኒያ አንድ አቻ ሲለያዩ÷ ዩክሬን እና ቤልጂየም ደግሞ ያለምንም ጎል ጨዋታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

የጨዋታውን ውጤት ተከትሎም ዩክሬን ከ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ተሰናባች ሀገር ሆናለች፡፡

በዚህም አራት ነጥብ ያላት ዩክሬን በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባ የተሰናበተች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

በሌላ በኩል በምድብ 6 የሚገኙት ፖርቹጋል ከጆርጂያ እንዲሁም ቱርክ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር ምሽት 4 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

ፖርቹጋል አስቀድማ ጥሎ ማለፉን ያረጋገጠች ሲሆን÷ ቱርክ ደግሞ አቻ መውጣት ብቻ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል ያስችላታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.