በ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር አትሌት ሳሮን በርሄ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድርን በማሸነፍ አትሌት ሳሮን በርሄ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡
እንዲሁም በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ውድድር አትሌት ንብረት መላክ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡
በካሜሩን ዱዋላ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 5 የወርቅ ሜዳሊያዎችን መሰብሰብ ችላለች፡፡
እስከ አሁን በተካሄዱ ውድድሮችም ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች የእርምጃ ውድድሮች 2 ወርቅ፣ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች 1 ወርቅና 1 ብር፣ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች 1 ወርቅና 1 ብር፣ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር 1 ወርቅ፣ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች 1 ብር፣ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሠናክል 1 ብር እንዲሁም በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች 1 ነሐስ በማግኘት በአጠቃላይ 5 የወርቅ፣ 4 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎችን መሰብሰብ ችላለች፡፡