Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሥተዳድር ም/ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባ በዘጠኝ ረቂቅ ደንቦች፣ አንድ ፖሊሲ እና ሁለት አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ የተወያየባቸው ጉዳዮችም÷ የመንገዶች ባለስልጣን ማቋቋሚያ ደንብ፣ የመንገድ ደኅንነት ምክር ቤት ማቋቋሚያ ደንብ፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፈንድ ማሥተዳደርና ማቋቋም የወጣ ደንብ፣ የስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ማቋቋሚያ ደንብ፣ የማሕበረሰብ ድጋፍ እና እንክብካቤ ጥምረት ማቋቋሚያ ደንብ፣ የአርባምንጭ ተሃድሶ ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ፣ በአርብቶ አደር አካባቢ የሚገኙ ሆስቴሎችን ማቋቋሚያ እና አጠቃቀም ደንብ፣ የቴክኒክና ሞያ ትምህርት ስልጠና የሥራ አመራር ቦርድ አደረጃጀት ለመደንገግ የወጣ ደንብ እና የቱሪዝም ገቢ አሰባሰብ ደንብ ናቸው፡፡

በቀረቡት ደንቦች ላይ የተወያየው ምክር ቤቱም ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆኑን በማመን ከነማሻሻያቸው ማጽደቁን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም ምክር ቤቱ ‘የወላይታ ግብርና ኮሌጅ ማቋቋሚያ አዋጅ’፣ ‘የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ማቋቋሚያ አዋጅ’ እና ‘የበጎ ፈቃደኝነት ረቂቅ ፖሊሲ’ ላይ በመወያየት ለክልሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.