Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ3 ሺህ ሜትር መሠናክል የሴቶች ውድድር የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሩን ዱዋላ በተካሄደው 3 ሺህ ሜትር መሠናክል የሴቶች ውድድር አትሌት ዓለምናት ዋለ ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች፡፡

በዚሁ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት መሠረት የሻነህ አራተኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት የሚጠበቁባቸው የ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የማጠቃለያ ውድድሮች እየተካሄዱ ነው፡፡

እስከ አሁን በተካሄዱ ውድድሮችም ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች የእርምጃ ውድድሮች 2 ወርቅ፣ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች 1 ወርቅና 1 ብር፣ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች 1 ወርቅና 1 ብር፣ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሠናክል 1 ብር  እንዲሁም በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች 1 ነሐስ በማግኘት በአጠቃላይ አራት የወርቅ፣ 3 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎችን መሰብሰብ ችላለች፡፡

በካሜሩን ዱዋላ በፈረንጆቹ ከሰኔ 21 ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው 23ኛው አፍሪካ አትሌቲክስ ሻፒዮና ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.