Fana: At a Speed of Life!

እስከ 470 ሚሊዮን ዶላር በሚደርስ ወጪ የጠጠር መንገድና ድልድዮች እንደሚገነቡ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪዎቹ 5 ዓመታት እስከ 470 ሚሊዮን ዶላር በሚደርስ ወጪ የጠጠር መንገድና ድልድዮች እንደሚገነቡ የከተማና መሰረተልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

መንገዶቹ የሚገነቡት በገጠር መንገድ ተደራሽነትና ትስስር ፕሮግራም ነው ተብሏል ።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)፤ የገጠር መንገድ ተደራሽነት ትስስር ፕሮግራም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ግብዓት በበቂ ሁኔታ ለገጠር አካባቢዎች ለማድረስ እንዲሁም የተመረተው ምርት ሳይባክን ለገበያ እንዲደርስ ያስችላል ብለዋል ።

ፕሮግራሙ ከአዲስ አበባ በስተቀር በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 128 ወረዳዎች ላይ የሚተገበር መሆኑን ጠቅሰው፤ 8 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ እና 1 ሺህ 200 ድልድዮች እንደሚገነቡ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በጂኦግራፊ የተለያዩ አካባቢዎችን በተንጠልጣይ ድልድዮች ማገናኘት የሚያስችሉ 374 ድልድዮች እንደሚገነቡ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ለፕሮጀክቱ ከ450 እስከ 470 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚደረግ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴዔታው÷ ይህም 30 በመቶ የሚሆነው በክልሎች የሚሸፈን ሲሆን 300 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ በዓለም ባንክ ይሸፈናል ነው ያሉት።

አሁን ላይ ለፕሮጀክቱ ትግበራ የመመሪያና የቴክኒካል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ በሚቀጥለው ዓመት ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ይገባል ብለዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.