Fana: At a Speed of Life!

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍን ለማሳደግ ስታርትአፕና ስትራይድ ኢትዮጵያ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍን ለማሳደግ ስታርትአፕና ስትራይድ ኢትዮጵያ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዘርፉ የተሰማሩ የግል እና የመንግስት አካላት በመደበኛ ሁኔታ የሚያገናኝ ማዕቀፍ ለመፍጠር ያለመ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት፣ የግል እና የመንግስት ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ በለጠ ሞላ (ዶ/ር)÷ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የግል ድርጅቶችን እምቅ አቅም በሚገባ ጥቅም ላይ ለማዋል የዘርፉን ማህበራት፣ የግልና የመንግስት ተቋማት የሚያገናኝ ማዕቀፍ መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ዘርፉን ለማሳደግ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የዘርፉ ማህበራት እና የልማት አጋሮች በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በተቋማቸው ይህንን ቅንጅት በማጠናከር ውጤታማ ስራ ለመስራት የስታርትአፕ እና ስትራይድ ኢትዮጵያን የመሰሉ መድረኮችን በመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ዘርፉን በማጠናከር ጉልህ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አንስተዋል።

በዝግጅቱ ላይ በዘርፉ የተሰማሩ የግልና የመንግስት ተቋማት በመደበኛነት በዘርፉ ጉዳዮችና ወደ ስራ ሲገባ ለሚፈጠሩ እንቅፋቶች የጋራ መፍትሄ ለማስቀመጥ የተዘጋጀ የማዕቀፍ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ተብሏል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የተሰጣቸውን ሃላፊነት ለመወጣት ዘርፉ የሚፈልገውን ቅንጅት በመፍጠር እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.