Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2017 ዕቅድ ዝግጅት ግምገማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአስፈጻሚ አካላት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2017 ዕቅድ ዝግጅት ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በበጀት ዓመቱ የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማጎልበት እንዲሁም መሻሻል ያለባቸውን በመለየት በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በጥልቀት በመገምገም መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች ማረም እንደሚገባ ገልጸው፤ በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ሥራዎችን መገምገም ማስፈለጉንም አንስተዋል፡፡

ዝርዝር የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ የተግባር አፈጻጸምም በመድረኩ እየቀረበ ሲሆን÷ በሚቀርበው ሪፖርት መነሻ ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ የክልሉ አስተባባሪ አካላትን ጨምሮ የክልሉ የሥራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.