በክልሉ ከ600 ኪ.ሜ በላይ የአስፓልት መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ነው-አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ከ610 ኪ.ሜ በላይ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ በመከናወን ላይ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ።
እንደ ርእሰ መስተዳድሩ ገለፃ በፌዴራል መንግስት ከተጀመሩ 612 ኪ.ሜ ርዝመት ካላቸው 9 የመንገድ ፕሮጀክቶች 6ቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ።
ቀሪዎቹ 3 ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አቶ ኡሞድ ገልፀዋል።
እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለፃ በራስ አቅም በወረዳዎች የመንገድ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በበጀት ዓመቱ ከ80 ኪ.ሜ በላይ የገጠር መንገድ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት በቅቷል።
በመራኦል ከድር