አካታችነትና ጥራት ያለው የትምህርት ሥርዓትን ለመገንባት ያለመ የፓን አፍሪካ ፓርላማ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አካታችነት፣ ጥራትና ዘላቂነት ያለው የትምህርት ሥርዓትን ለመገንባት ያለመ 6ኛው የፓን አፍሪካ ፓርላማ 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ሚድራንድ መካሄድ ተጀምሯል።
ጉባኤው “አካታች፣ ጥራት ያለው፣ ተገቢ እና ዘላቂነት ያለው የትምህርት ሥርዓትን መገንባት” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት ርዕሰ ጉዳይም “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ትምህርት ለአፍሪካውያን አካታች፣ ጥራት ያለው፣ ተገቢ እና ዘላቂነት ያለው የትምህርት ሥርዓትን መገንባት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጉባኤው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እስከ ፈረንጆቹ ሐምሌ 5 ቀን 2024 የሚቀጥል ይሆናል ነው የተባለው።
በጉባኤው የተለያዩ አለምአቀፍና የአፍሪካ ተወካዮች፣አምባሳደሮች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተው የድጋፍና የአጋርነት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
በጉባኤው የኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣አምባሳደሮች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።