Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ የሶማሌ ክልል የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን 47 በመቶ መድረሱን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በሶማሌ ክልል ያለው የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን ከ19 ወደ 47 በመቶ ማሣደግ መቻሉን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አስታወቁ፡፡

ከለውጡ ወዲህ ከ15 በላይ ከተሞችን ተጠቃሚ ያደረጉ ከ300 በላይ የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክቶች አገልግሎት መስጠታቸውንም አቶ ሙስጠፌ አብራርተዋል፡፡

በዚህም የክልሉ ንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ሽፋን ከ19 ወደ 47 በመቶ አድጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ፍላጎቶችን ለመመለስ አሁንም ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚያስፈልጉ አመላክተው÷ ይህን ታሳቢ ያደረጉ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

ከኤሌክትሪክ አገልግሎት አኳያም ከለውጡ ወዲህ ከፍተኛ የአገልግሎት ማስፋፊያ ሥራ ተከናውኗል ብለዋል፡፡

ለአብነትም 20 ወረዳዎች የ24 ሠዓት እና 70 ከተሞች በከፊል የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.