Fana: At a Speed of Life!

የቱርክ እና የሩሲያ ፕሬዚዳንቶች በቀጣይ ሳምንት ይወያያሉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን እና የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቀጣይ ሳምንት እንደሚወያዩ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የሁለቱ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች በሚቀጥለው ሳምንት በካዛኪስታን በሚካሄደው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት (ኤስሲኦ) ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ከስብሰባው ጎን ለጎን እንደሚወያዩ አረጋግጠዋል።

ኤርዶሃን እና ፑቲን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ስለገባችበት ጦርነት እና በጥቁር ባህር በኩል የእህል እንቅስቃሴ ለመጠበቅ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ እንደሚወያዩ አርቲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም የተፈጥሮ ጋዝ የንግድ ማዕከል መመስረት፣ የቱርክ አኩዩ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ እና በሶሪያ የኩርድ ክልሎች ስለሚካሄደው ምርጫ ላይ ይወያያሉ ነው የተባለው፡፡

የኤስሲኦ ስብሰባ በፈረንጆቹ ሐምሌ 3 እና 4 ቀን 2024 በካዛኪስታን አስታና እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.