1 ሺህ 175 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 175 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡
የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ ከእነዚህ ውስጥም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 20 ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡