Fana: At a Speed of Life!

በሩሲያ በደረሰ የእሳት አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሩሲያ መዲና ሞስኮ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የቀድሞ የምርምር ተቋም ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ እስካሁን የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በአደጋው ሁለት ሰዎች እሳቱ በድንገት ከተነሳ በኋላ ማምለጥ ባለመቻላቸው ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉ ተጠቁሟል፡፡

ቀሪዎቹ ደግሞ በቃጠሎው ሳቢያ በተከሰተ የሕንጻ መደርመስ ለሕልፈት መዳረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡

በማህበራዊ ትስስር-ገጾች ላይ በተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስልም ባለ ስምንት ፎቅ የሆነው የቀደሞ የምርምር ተቋም ሕንጻ በእሳት ሲቀጣጠል ታይቷል፡፡

እሳቱን ለማጥፋት የነፍስ አድን ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ የአካባቢው የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ማስታወቁንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.