Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቀሪና ድጋሚ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ ነው፡፡

በዚህ መሰረትም በክልሉ ዳንጉር ምርጫ ክልል ለተካሄደው ምርጫ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በምርጫ ክልሉ 33 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ በ32 ጣቢያዎች ላይ መራጮቸ የምርጫውን ውጤት ማወቃቸው ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ መሰረት አንካሽ ቡርጂ ምርጫ ጣቢያ ላይ ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ የምርጫ ሒደቱ መቀጠሉ ተጠቅሷል።

የምርጫ ሒደቱ ነጻ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ እንደሆነም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.