በጅግጅጋ ምርጫ ክልል 2 ሲካሄድ የዋለው ድጋሚ ምርጫ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ምርጫ ክልል ሁለት ዛሬ ሲካሄድ የዋለው ድጋሚ ምርጫ መጠናቀቁን የምርጫው አስተባባሪ አስታወቁ።
የምርጫው አስተባባሪ አቶ ሃይለየሱስ ወርቁ እንደገለጹት፥ በከተማው በተቋቋሙ 123 ምርጫ ጣቢያዎች ህዝቡ ያለምንም ችግር በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚፈልገውን ዕጩ መርጧል።
ምርጫው መጠናቀቁን ተከትሎ አሁን ላይ የምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች በተገኙበት በየምርጫ ጣቢያው የድምፅ ቆጠራ መጀመሩን የዘገበው ኢዜአ ነው።