የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሚያከናውናቸውን ችግር ፈቺ ሥራዎች እንዲያጠናክር ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሚያከናውናቸው ችግር ፈቺ ሥራዎች አስደሳች መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ጠየቁ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስኬቶችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ እየተገነቡ የሚገኙ የፎረንሲክ ሣይንስ ኢንስቲትዩትና ባለ አምስት ኮከብ የኢንተርናሽናል ፖሊስ ሊደርሽፕ ኢንስቲትዩት ፕሮጀክቶች በምን ደረጃ ላይ እንዳሉሉ ተመልክተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሌሎች በሪፎርሙ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥኬታማ ተግባራትን መጎብኘታቸው ነው የተገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና የምርምር ተቋማትን በመገንባትና የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት ረገድ እየሠራ ያለውን ውጤታማ ተግባር ተዘዋውረው መመልከታቸውም ተጠቁሟል፡፡
አቶ አሕመድ ሽዴ ፥ የፎረንሲክ ሳይንስ ኢንስቲትዩትና ባለ አምስት ኮከብ የኢንተርናሽናል ፖሊስ ሊደርሽፕ ኢንስቲትዩት ፕሮጀክቶች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው የአከባቢውን ማህበረሰብ ችግር ለመፍታት እየሠራ ያለው ተግባር አስደሳች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህም የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግለጻቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡