ፖርቹጋል ጥሎማለፉን መቀላቀሏን አረጋገጠች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛው ዙር ጨዋታ ፖርቹጋል ቱርክን 3 ለ 0 አሸንፋለች።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ፖርቹጋል ቱርክን በበርናርዶ ሲልቫ፣በቡሮኖፈርናንዴዝ እና በአካይዲን (በራሱ መረብ ላይ) ጎሎች 3 ለ 0 ረትታለች፡፡
በዚህም ፖርቹጋል ጥሎማለፉን መቀላቀሏል አረጋግጣለች፡፡
እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ላይ በምድብ 5 የተደለደሉት ሮማንያ እና ቤልጂየም ይጫወታሉ፡፡
ሮማንያ ምድቡን በቀዳሚነት ስትመራ ቤልጂየም በአንጻሩ በምድቡ መጨረሻ ላይ ትገኛለች፡፡
በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 ስትረታ÷ ቤልጂየም በስሎቫኪያ 1 ለ 0 መሸነፏ ይታወሳል፡፡