Fana: At a Speed of Life!

የኮንስትራክሽን ብረታ ብረት ሲሰርቁ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግል ድርጅት የኮንስትራክሽን ብረታ ብረት ሲሰርቁ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የተባሉ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:30 ከጥበቃ ሰራተኞች ጋር በመተባበር በአይሱዙ ተሽከርካሪ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ብረታ ብረቶችን ጭነው ሊሰወሩ ሲሉ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ኢንተለጀንስ ባለሙያዎች እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ነው የተባለው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.