በትግራይ ክልል ከ35 ሺህ ሔክታር በላይ የሚሸፍን የተከላ ቦታ ካርታ ተዘጋጀ On Jun 22, 2024 116 አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ አሁን ከ35 ሺህ ሔክታር በላይ የሚሸፍን የተከላ ቦታ ካርታ መዘጋጀቱን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ለሚተከሉ ችግኞች እንክብካቤና ጥበቃ ለማድረግ ካርታ እየተዘጋጀ መሆኑን በቢሮው የደን ልማትና አጠቃቀም ዳይሬክተር ተስፋይ ተክለሃይማኖት ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ ዘንድሮ በዳገታማና ለደን ተብለው በተከለሉ ሥፍራዎች ጭምር ችግኝ እንደሚተከል ገልጸው÷ ከ22 ሺህ ሔክታር በላይ የደን ቦታዎች ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ነፃ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡ 116 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint