Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የመንግስትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጉባ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስት የሠላምን ጥሪ በመቀበል ከነሙሉ ትጥቃቸው ተመልሰው ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለዋል።

የክልሉ መንግስት ወደዘላቂ ሠላም ለመመለስ ባደረገው ስምምነት መሠረት 10 የሠላም ተመላሽ ታጣቂ አመራር እና 129 የታጣቂ አባላት በአጠቃላይ 139 ታጣቂዎች የሠላሙን አማራጭ በመምረጥ የገቡ ሲሆን÷ ትጥቃቸውን ሙሉ ለሙሉ ለመንግስት አስረክበዋል።

የሀሳብ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት የግጭት መንስኤ የሆኑትን አጀንዳዎች በማስቀረት የክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማስቀጠል በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል።

ከዓመታት በፊት የተመለሱ ሠላም ተመላሾች በተለያዩ የሥራ መሥኮች ተሠማርተው ሀገራቸውንና ራሳቸውን እየለወጡ እንደሆነና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የአካባቢያቸውን ሠላም በማስጠበቅ ወደ ልማት ገብተው እየሠሩ እንደሚገኙም ተመላክቷል።

በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የፀጥታ አመራሮች ተገኝተው ደማቅ አቀባበል መደረጉን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በቅርቡ ከቀሪ የታጣቂ ቡድን አመራሮችና አባላት ጋር በሠላማዊ ትግል ዙሪያ በመወያየት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.