Fana: At a Speed of Life!

በቦንጋ ከተማ ለሚገነባው የመደመር ትውልድ ቤተ መጽሐፍት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በቦንጋ ከተማ ለሚገነባው የመደመር ትውልድ ቤተ መጽሐፍት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልል ደረጀ በቦንጋ ከተማ የሚገነባው የመደመር ትውልድ ቤተ መጽሐፍት ከመጽሐፉ ሽያጭ በሚገኝ ገንዘብ የሚሰራ ነው፡፡

የቤተ መጽሐፍቱ ፕሮጀክት ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በሚገኝ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚከናወን ባለ አንድ ወለል ሕንጻ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ግንባታውን የሚያከናውነው የክልሉ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬት ሥራውን በተሻለ ጥራት ደረጃ እና በተያዘለት የጊዜ ገደብ አጠናቆ እንዲያስረክብ ማሳሰባቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.