Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የማይክሮ አልጌ ምርምርና ማምረቻ ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የማይክሮ አልጌ ምርምርና ማምረቻ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነው የማይክሮ አልጌ (ስፓይሩሊና) ምርምርና ማምረቻ ማዕከል ተመርቋል፡፡

ማዕከሉ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ነው የተገነባው፡፡

ባለፉት 3 ዓመታት የምርምርና የልማት ሥራው ሲጠና የቆየው የምርምር ማዕከሉ ግንባታው ተጠናቅቆ አዳሚ ቱሉ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

1 ሺህ 200 ካሬ ሜትር ላይ ግንባታው ያረፈው የምርምር ማዕከሉ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የግንባታ ወጪ የተደረገበት ሲሆን÷ በወር ከ30 ኪሎ ግራም በላይ ማይክሮ አልጌ ማምረት እንደሚችል ተነግሯል።

የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ካሳሁን ተስፋዬ (ፕ/ር) ÷ኢንስቲትዩቱ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ምርምሮች በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያላት የስፓይሮሊና ሃብት የሕጻናት የመቀንጨር ችግርን ለመቀነስ ተግባራዊ ይደረጋል ማለታቸውንም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የስፖይሮሊና ምርምርና ማምረቻ ማዕከል እንደሀገር የሥነ ምግብ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ የተገኘውን ውጤት የበለጠ ከፍ ለማድረግ አጋዥ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.