ሩሲያና ቬትናም ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ቃል ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያና ቬትናም ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ቃል መግባታቸው ተገልጿል፡፡
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለይፋዊ ጉብኝት ቬትናም መግባታቸው ይታወቃል፡፡
ቭላድሚር ፑቲን እና አቻቸው የቬትናም ፕሬዚዳንት ቶ ላም በቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም ፥ የሀገራቱን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ቃል መግባታቸው ተነስቷል፡፡
ፑቲን በዚህ ወቅት ፥ ከቬትናም ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ማጠናከር በሩሲያ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው ብለዋል።
ቬትናም አሁንም ከሩሲያ ጋር ያላትን ጠንካራ ግንኙነት ዋጋ እንደምትሰጥ ትገልጻለች እንደ ቢቢሲ ዘገባ፡፡
ለዚህም ማሳያ ከብዙ ዓመታት በፊት ሩሲያ በወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ይነሳል፡፡
በዚህም ቬትናም ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ስትገልጽ በመተማመን የተሞላ ነው ትለዋለች፡፡