Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 11 ወራት 171 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ኮሚሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት11 ወራትት 171 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት እድገት ያለበትን ደረጃ እንዲሁም የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ ቀናት ስራ ክንውንን በሚመለከት ውይይት አካሂዷል፡፡

በዚሁ ወቅት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ÷ውይይቱ የተሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ላጋጠሙ ችግሮች መፍትሔ ለማበጀት እንዲሁም ለ2017 የበጀት ዓመት እቅድ ግብዓት ለመሰብሰብ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

በ2016 የበጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት 191 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እንደታቀደና 171 ነጥብ 4 ቢሊየን መሰብሰብ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

የገቢ አሰባሰቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር እድገት አሳይቷል ተብሏል፡፡

ባለፉት 11 ወራትም 9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የገቢ እና 4 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የወጭ በድምሩ 14 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.