አቶ ደስታ ሌዳሞ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የክልሉን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ለኩ ከተማ አስጀምረዋል።
አቶ ደስታ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት÷ በዘንድሮው ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 2 ሺህ ቤቶችን ለማደስ እቅድ ተይዟል፡፡
ተግባሩ በአንድ ጊዜ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ አለመሆኑን ጠቁመው÷ ለትውልድ በጎ ማድረግ መልካም እሴት መሆኑንና በትውልድ የሚቀጥል ተግባር መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም አቅም ያለው አቅም ለሌላቸው እንዲያካፍልና የተቸገሩትን መርዳት እንደሚገባው ፤በጎነትንም የየቀን ተግባር ማድረግ እንደሚስፈልግ ማውሳታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የዘንድሮው የበጎ ተግባር ሥራ በሁሉም አከባቢዎች በተለያዩ የሥራ ተግባራት አቅም ያላቸው በአቅማቸውና ወጣቶች በጉልበታቸው በመደገፍ የማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡