Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለምታደረግው ጦርነት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ የገቡት የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን በወታደራዊ ትርዒት የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፑቲን ባለፈው መስከረም ወር ኪም ጆንግ ኡን ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነው ከ24 ዓመታት በኋላ ወደ ሰሜን ኮሪያ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያቀኑት፡፡

ሁለቱ መሪዎች በነበራቸው ውይይትም ሀገራቱ ያላቸውን ወታደራዊ ትብብር ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በአሁኑ ወቅት ከዩክሬን ጋር በጦርነት ውስጥ ለምትገኘው ሩሲያ ሰሜን ኮሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ ኪም ጆንግ ኡን ገልጸዋል።

በተለይም ሁለቱ የኒውክሌር ሃይል የታጠቁ ሀገራት በዘርፉ ያላቸው ትብርብ ይበልጥ ለማጠናከር መምከራቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም ሁለቱ መሪዎች በኢኮኖሚ እና በሌሎች መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ መወያየታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ኪም ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለምታደርገው ጦርነት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.