Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሠላም ቀጣይነት እየሠራች ነው – ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለቀጣናውና ለአፍሪካ ሠላም ቀጣይነት ባለው መልኩ ስትሠራ መቆየቷንና አሁንም ብዙ ዋጋ እየከፈለች መሆኗን የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ገለጹ።

በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ በተጀመረው የብሪክስና አጋር ሀገራት ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) “undivided and equal security as a key principle for building genuine and lasting international peace” በሚል የውይይት መድረክ ላይ ፓርቲያቸውን ወክለው ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ኢትዮጵያ ለቀጣናውና ለአፍሪካ ሠላም ቀጣይነት ባለው መልኩ ስትሠራ የቆየችና አሁንም ብዙ ዋጋ እየከፈለች መሆኑን አውስተዋል፡፡

ለዚህ ማሳያነት የፀጥታ ችግር በገጠማቸው የአፍሪካ ሀገራት ሁሉ ኢትዮጵያ ከጎናቸው ነበረች ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የሩሲያ መንግሥት በማንኛውም አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ላሳየው አጋርነት አመስግነው÷ ይኸው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የብሪክስ መድረክ ሀገራትም ለሠላማቸው በጋራ የሚተባበሩበት እንዲሆን እምነታቸውን ገልፀዋል።

በተለይም ለሠላም ጠንቅ የሆነውን ድህነትና ኋላቀርነት ለማስወገድ የብልፅግና ፓርቲ በትኩረት እየሠራና አበረታች ውጤት እያስመዘገበ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ለዚህም የብሪክስ አባል ሀገራት በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት መንፈስ ሊሠሩ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.